habeshatimes.com
የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝብ ሁለት ህዝብ ነው ብለው የሚገልፁ ሀቁን የማያውቁ ብቻ ናቸው- ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ | HT
የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፥ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የክልል ርእሳነ መስተዳድራን፣ ሚኒስትሮች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና የጥበብ ሰዎች ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አርገውላቸዋል። ፕሬዚዳንቱ በብሄራዊ ቤተመንግስት በተደረገላቸው የምሳ ግብዣ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፥ የኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝብ ለሰላም ያለው...