kalitipress.com
በወንዞች ዳርቻ ልማት 30 ሺሕ ነዋሪዎች ይነሳሉ - Kaliti Press
በሃያ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ወጪ ይከናወናል የተባለው የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻዎች ልማት ፕሮጀክት 30 ሺሕ ነዋሪዎችን እንደሚያስነሳ ተገለጸ፡፡ ከእንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ከተማዋን ለሁለት ከፍለው በሚፈሱ ወንዞች ዙሪያ ሰፍረዋል የተባሉትን 30 ሺሕ ነዋሪዎች መልሶ ለማስፈር እንቅስቃሴ መጀመሩን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የቴክኒክ አማካሪ ወ/ሮ መስከረም ታምሩ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ሃምሳ ስድስት ኪሎ ሜትር በሚሸፍነው