kalitipress.com
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከሰሙኝ..... (ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)
በእርግጥ ጊዜ የለዎትም። እርስዎ ይለፋሉ። ስለሀገር ወዲህና ወዲያ ሲሉ ጊዜ እንደማይኖርዎት አውቃለሁ። ምናልባት የእርስዎን የማህበራዊ መድረክ ጉዳዮች የሚመለከተው አካል ይህ መልዕክቴን በአጋጣሚ ካገኘው ለእርስዎ ሹክ ቢያደርግልኝ ደስ ይለኛል። እርስዎን ተንጠልጥለው፡ እርስዎ ያገኙትን እውነተኛ የህዝብ ፍቅር እንደመሰላል ተጠቅመው፡ ቆሻሻቸውን ሳያርግፉ፡ ከነጉድፋቸውና ሃጢያታቸው ርካሽ ጥቅምና ተወዳጅነት ፍለጋ የሚክለፈለፉትን ባየሁ ጊዜ ማለፍ ስላቃተኝ ነው ይህ መጣጥፍ ከደ