kalitipress.com
ከ2 ሺህ በላይ ብስክሌቶች ከአራት ዓመታት በላይ ያለጥቅም መጋዘን ውሰጥ ተከማችተዋል
የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለአማራ ክልል ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የሚረዱ ከ2 ሺህ በላይ ብስክሌቶች ለክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ከአራት ዓመታት በፊት መስጠቱ ተዘግቧል፡፡ የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮም ብስክሌቶቹን ከሶስት ዓመታት በላይ ለጸሃይና ለዝናብ አጋልጧቸው ቆይቷል፡፡ ከአንድ አመት በፊት ደግሞ የዓለም አቀፍ ኦዲተሮች መምጣታቸውን ተከትሎ ያለመጠለያ ተሠጥተውበት ከነበረው ሜዳ በማራቅ አባይ ማዶ ወደሚገኝ መጋዘን እንደተለመደው ያለስርዓት እንዲደረደሩ ተደርገ