kalitipress.com
“በአንዳርጋቸው እግር ስር ወድቄ ረጅም ሠዐት መነሳት ተስኖኝ ነበር” እየሩሳሌም ተስፋው
ግዮን፡- በግንቦት ሰባት ታስራችሁ ከረጅም ጊዜ እስር በኋላ ስትፈቱ የክሳችሁ ዋና መነሻ የነበረው አንዳርጋቸው ጽጌ በወቅቱ አለመፈታቱን ስታውቁ ምን ተሰማሽ? እየሩሳሌም፡- እኔ እስሬን ጨርሼ ነው እንጂ የወጣሁት በምህረቱ አይደለም:: እኔ ከመውጣቴ አንድ ወር በፊት ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይለቀቃሉ የሚለውን ነገር ሰምቻለሁ:: በፍጹም አዕምሮዬ ውስጥ አንዳርጋቸው ይወጣል የሚል እምነት መቼም አልነበረኝም:: አሁን ስወጣ ሳየው ነው ያረጋገጥኩት እንጂ እስከመጨረሻው ሠ