kalitipress.com
ምን ሰወራት?! (የትነበርክ ታደለ)
....ምንም ቆንጆ ብትሆን የሚኮሰኩስ ጸባይ ያላት ሴት በጣም ነው የምታስጠላኝ! የምትኮሰኩሰኝ ሴት ደግሞ በሰፈሩ ያለኔ ቆንጆ የለም የምትል አይነት...ይህንንም በአካሄዷም፣ በአነጋገሯም በቃ በሁሉ ነገሯ እኔን ብቻ እዩኝ! እናንተ አስቀያሚዎች!" የሚል መልእክት በሁኔታዋ ሁሉ ለማስተላለፍ ትሞክራለች። እና ደስ አትልም! ....ክፉ እድል ሆነና እንዲህ አይነት ልጅ ያለችበት ግቢ ውስጥ ቤት ተከራየሁ።.....አቤት እዳዬ?! እስኪ አሁን በኔ ላይ ምን እንዲህ ያደርጋታል?